የD.C. የአስተዳደራዊ ችሎት ቢሮ (ኦፊስ ኦፍ አድሚኒስትሬቲቭ ሂሪንግ) እንደ አስተዳደር ፍርድ ቤት ሆኖ የሚያገለግል ገለልተኛ ድርጅት ነው። “የአስተዳደር ፍርድ ቤት” የመንግስት ስራ አስፈጻሚ አካል ነው እና በዋናነት የመንግስት ድርጅት ውሳኔዎችን እና በግለሰቦች ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎችን በሚያካትቱ ጉዳዮች ላይ ያተኩራል። እንደ ገለልተኛ ድርጅት፣ OAH ውሳኔውን ከሚወስኑ ወይም በግለሰቦች ላይ እርምጃ ከሚወስዱ ድርጅቶዎች ይለያል እና በማንኛውም ጉዳይ ገለልተኛ ነው።
OAH ድርጅቱን ለሚነጋግር ወይም የችሎት ሂደቱን ለሚያካሂድ ለማንኛውም ሰው ነጻ የትርጉም አገልግሎት ይሰጣል። ለችሎት ወይም ለሽምግልና አስተርጓሚ ከፈለጉ፣ እባክዎ በተቻለ ፍጥነት ያሳውቁን። የችሎት ጥያቄ በሚያቀርቡበት ጊዜ፣ ወይም በሌላ በማንኛውም ጊዜ ለOAH በ (202) 442-9094 በመደወል ወይም [email protected] ኢሜይል በማድረግ አስተርጓሚ መጠየቅ ይችላሉ።
በእርስዎ ችሎት ቀን አስተርጓሚ ካልተጠየቁ፣ አስተርጓሚ እንደሚያስፈልግዎት ለዳኛው ማሳወቅ አለብዎት፣ እና ዳኛው አስተርጓሚ እንዲያገኝልዎት ሊሞክር ይችላል። ዳኛው ወዲያውኑ አስተርጓሚ ማግኘት ካልቻለ፣ ዳኛው OAH ለአዲስ የችሎት ቀን አስተርጓሚ እንዲያዘጋጅ ጊዜ ለመስጠት ችሎቱን ለሌላ ጊዜ ማስተላለፍ ይኖርበታል።
እንዲሁም በአካል በመገኘት ወይም በስልክ በመደወል፣ ከOAH የደንበኛ አገልግሎት ተወካይ ወይም ከመረጃ ማዕከል ሰራተኛ ጋር መነጋገር ካስፈለገዎ፣ OAH አስተርጓሚ ማቅረብ ይችላል። በሚጎበኙበት ወይም በሚደውሉበት ጊዜ፣ በቀላሉ አስተርጓሚ ይጠይቁ እና ቋንቋዎን ይለዩ፣ እና የOAH ሰራተኞች ለእርዳታ አስተርጓሚውን ያነጋገራሉ።
ከOAH ሰነዶችን በእንግሊዘኛ ቋንቋ ከተቀበሉ እና እንዲተረጎሙ ከፈለጉ፣ እባክዎ (202) 442-9094 ይደውሉ ወይም በአካል እርዳታ ለማግኘት OAHን ይጎብኙ።
የOAH የተሻሻለ የአሰራር የጊዜ ሰሌዳ
የአስተዳደራዊ ችሎት ቢሮ (ኦፊስ ኦፍ አድሚኒስትሬቲቭ ሂሪንግ) በተሻሻለ የአሰራር የጊዜ ሰሌዳ ክፍት ነው። የድርጅቱ ሰአታት ከሰኞ እስከ አርብ፣ 9:00 am – 5:00 pm ናቸው። ነገር ግን፣ OAH ያለ ቀጠሮ ለሚጎበኙ ከሰኞ እስከ አርብ፣ ከ9:00 am – 12:00 pm፣ እና 1:00 pm – 5:00 pm ብቻ ክፍት ነው። በስራ ሰአታት ነገር ግን OAH ያለቀጠሮ ለሚጎበኙ ዝግ በሚሆንበት ሰዐት ከደረሱ፣ የፊት ለፊት መግቢያው ዝግ ይሆናል፣ ነገር ግን ወረቀቶችን ማቅረብ ወይም በአካል ተገኝተው ችሎት መመዝገብ ይችላሉ። ወረቀቶችን ለማስገባት እና ችሎት ለመመዝገብ መመሪያዎች ከፊት ለፊት መግቢያው ውጪ ባሉት ጠረጴዛዎች ላይ ይገኛሉ።
የOAH ቅጾች
የችሎት መጠየቂያ ቅጾች
- ለህግ ጥሰት ማስታወቂያ ወይም ለስምምነት መፍረስ ማስታወቂያ መልስ
- ስራ የማቆም ትዕዛዙን በሚመለከት ከዲፖርትመንት ኦፍ ቢውልዲንግስ (DOB) የመጨረሻ ውሳኔ ይግባኝ
- ስለ የታክሲካብ (Taxicab) ወይም ፎር-ሃየር-ቬሂክል (For-Hire Vehicle) ትኬት ለመከራከር የሰሚ ችሎት መጠየቂያ
- በህዝብ ጥቅማጥቅሞች ጉዳዮች የአስቸኳይ ጌዜ ክርክር መስማት (ችሎት) ይጠይቁ
- በባህሪ ጤና (Behavioral Health) የተወሰደ ውሳኔን ወይም እርምጃ ይግባኝ መጠየቂያ
- በህጻናት ድጋፍ አገልግሎቶች ክፍል (CSSD) የተወሰደ የማስፈጸሚያ እርምጃን ይግባኝ መጠየቂያ
- የመሳሪያ ምዝገባ የምስክር ወረቀትን በሚመለከት በከተማ ፖሊስ መምሪያ (MPD) የተወሰነውን ውሳኔ ይግባኝ መጠየቅ
- የደህንነት መኮንን ማረጋገጫን በሚመለከት በከተማ ፖሊስ መምሪያ (MPD) የተወሰነውን ውሳኔ ይግባኝ መጠየቅ
- የተደበቀ የእጅ ሽጉጥ ፈቃድን በሚመለከት በሜትሮፖሊታን ፖሊስ መምሪያ (MPD) የተደረገ ውሳኔ ላይ የይግባኝ መጠየቅ
- በሃይልና አካባቢ ክፍል (Department of Energy and Environment (DOEE)) የዝቅተኛ ገቢ የቤት ሃይል ድጋፍ መርሃ-ግብር (Low Income Home Energy Assistance Program (LIHEAP)) በሚመለከት የተሰጠ ውሳኔን ይግባኝ መጠየቂያ
- በሰው አገልግሎቶች (Department of Human Services (DHS)) የተወሰደ እርምጃን ይግባኝ መጠየቂያ
- በዕክል ያለበት ግለሰብ አገልግሎቶች (Disability Services) ውሳኔ ወይም እርምጃን ይግባኝ መጠየቂያ
- በጤና ክብካቤ ክፍል (Department of Health Care Finance (DHCF)) ወይም በዲኤችሲኤፍ (DHCF) ኮንትራክተር የሜዲኬይድ ሽፋን (Medicaid Coverage) የተወሰደ ውሳኔን ወይም እርምጃን ይግባኝ መጠየቂያ
- በሰው አገልግሎቶች ክፍልን (Department of Human Services (DHS)) ወይም በዲኤቼስ አቅራቢን (DHS Provider) የኪራይ ድጋፍ (Rental Assistance Decision) ውሳኔ ወይም እርምጃ ይግባኝ መጠየቂያ
- መጠለያን (Shelter) በሚመለከት የተሰጠ ውሳኔን ወይም እርምጃ ይግባኝ መጠየቂያ
- የቀረበው ግምገማ ላይ የግብር ከፋይ ተቃውሞ
- የስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች ይግባኝ ቅጽ
- የDepartment of Health Care Finance (DHCF) በMedicaid አቅራቢ ላይ ላሳለፈው ውሳኔ የይግባኝ ጥይቄ
- የልዩ ትምህርት የክፍያ ደረሰኝ ሙግት/የክፍያ አለመስጠት የይግባኝ ቅጽ
ሁሉም ሌሎች ቅጾች
- የጉዳይ ማህደሮችን ለመልቀቅ ስልጣን
- የእውቂያ መረጃ ለውጥ ጥያቄ
- የፎርም ማስረከቢያ ቅጽ
- የአገልግሎት የምስክር ወረቀት
- ለአገልግሎት ፈቃድ በኢሜይል
- የማቅረብ ሽፋን ሉህ
- የጊዜ ማስታወቂያ
- የጊዜ ማስታወቂያ እና የህግ ተማሪ እና የተቆጣጣሪ ጠበቃ ማረጋገጫ
- የገጽታ ማስታወቂያ (ጠበቃ ላልሆነ)
- የተለየ የችሎት ቀን ጥያቄ
- የአዲስ ችሎት ጥያቄ (“ችሎቴ አምልጦኛል”)
- የመቆየት ጥያቄ
- የመጥሪያ ጥያቄ
- የኪራይ ቤት ጉዳይ መጥሪያ
- በስራ አጥ ጥቅማጥቅሞች ጉዳይ ላይ የመጥሪያ ጥያቄ
- የችሎት ድምጽ ለመቅዳት መጠየቅ
- በ DCPS ጉዳይ የችሎት ድምጽ ለመቅዳት መጠየቅ
- የፍርድ ቤት ሰነዶችን ወይም መዝገቦችን ለማየት ይጠይቁ
- የግኝት ጥያቄ
- የቪዲዮ ኮንፈረንስ ወይም የአካል ችሎት ይጠይቁ
- የመጨረሻ ውሳኔን የመለወጥ ጥያቄ
- በስልክ ለመሳተፍ ይጠይቁ
- በተቀማጭ ላይ የመገኘት እና የመመስከር መጥሪያ
- በችሎት ላይ ለመገኘት እና ለመመስከር መጥሪያ
- ሰነዶችን፣ መረጃዎችን፣ ወይም እቃዎችን ለማዘጋጀት መጥሪያ። ወይም ምርመራ ለመፍቀድ
ቅጽ እንዴት ማቅረብ ይቻላል
በአካል እንዴት ማቅረብ ይቻላል
OAH የት ይገኛል?
OAH በ One Judiciary Square ህንጻ (“Marion S. Barry, Jr. ህንጻ” ተብሎም ይጠራል) በ 441 Fourth Street, Northwest ውስጥ ነው። ህንጻው የሚገኘው ከ Judiciary Square Metro stop (“4th Street/U.S. and D.C. Courthouses” መውጫ) በላይ በ Red Line ላይ ነው። እንዲሁም የD6 ሜትሮ አውቶቢስ በአራተኛው እና E Streets Northwest መታጠፊያ አቅራቢያ ይቆማል። የሚነዱ ከሆነ፣ የክፍያ ጎዳና መኪና ማቆሚያ ቦታ ማግኘት ወይም በአካባቢው ለሚገኝ የመኪና ማቆሚያ ጋራዥ መክፈል አለብዎት OAH ነጻ የመኪና ማቆሚያ ወይም የተረጋገጠ የመኪና ማቆሚያ የለውም።
አንዴ ህንጻውን ካገኘሁ በኋላ OAHን እንዴት ማግኘት እችላለሁ?
OAH በ Suite 450 North ውስጥ ነው፣ ማለትም OAH በህንጻው የሰሜን አቅጣጫ፣ አራተኛው ፎቅ ላይ ነው። እዚያ ለመድረስ፣ በፊት ለፊት የህንጻው መግቢያ ይግቡ እና ወደ ደህንነት ማረጋገጫ ቦታ ይሂዱ። ወደ ብረት ጠቋሚ ለማለፍ የደህንነት ጥበቃ መመሪያዎችን ይከተሉ። ደህንነቱን ለማለፍ፣ እንደ የመንጃ ፍቃድ ያለ፣ የፎቶ መለያ ያስፈልግዎታል። ደህንነቱን ካለፉ በኋላ፣ ለአሳንሰሮች "በሰሜን መተላለፊያ" ውስጥ ወደ ግራ ይሂዱ። ወደ አራተኛ ፎቅ አሳንሰር ይያዙ፣ እና ከአሳንሰሩ ሲወርዱ የ OAH መግቢያ ይመለከታሉ። ሁለት መስታወት ወዳላቸው በሮች ይሂዱ እና በፊት ዴስክ ላይ ላሉት ሰራተኞች የሆነ ነገር ማቅረብ እንደሚፈልጉ ያሳውቋቸው።
በመደበኛ የስራ ሰአታት በአካል ማቅረብ ይችላሉ፦ ከበአላት በስተቀር፣ ከሰኞ እስከ አርብ፣ 9:00 AM to 5:00 PM ነገር ግን፣ OAH በአሁን ጊዜ ያለ ቀጠሮ ለሚደረጉ ጉብኝቶች የአሰራር የጊዜ ሰሌዳውን አሻሽሏል። በስራ ሰአታት ከደረሱ፣ ነገር ግን OAH ያለ ቀጠሮ ለሚደረጉ ጉብኝቶች ዝግ በሆነበት ጊዜ ከሆነ፣ አሁንም ከመግቢያው በውጪ በኩል በሚገኘው ግራጫ የድራፕ ቦክስ ወረቀቶችን ማስገባት ይችላሉ። ደረጃ በደረጃ ያሉ መመሪያዎች ከሁለቱ በሮች አጠገብ ባለው ጠረጴዛ ላይ ይገኛሉ።
በፖስታ እንዴት ማቅረብ ይቻላል
ወረቀቶችን ወደዚህ አድራሻ በፖስታ ማስገባት ይችላሉ፦
Clerk’s Office
D.C. Office of Administrative Hearings
441 Fourth Street NW, Suite 450 North
Washington, DC 20001
አንድ ወረቀት በፖስታ ከላኩ፣ ወረቀቱ በOAH በመደበኛ የስራ ሰአታት ወቅት በተቀበለበት ቀን “እንደገባ” ይወስደዋል። ወረቀቱ በላኩበት ቀን “አይገባም”። ይህ በጣም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፣ በተለይ ወረቀትዎን በመጨረሻ ቀን ወይም ከመጨረሻው ቀን ቀድመው በፖስታ የሚያስቀምጡ ከሆነ – ወረቀትዎ የመጨረሻው ቀን በሚሞላበት ጊዜ በOAH ላይደርስ ይችላል። ደብዳቤው ረጅም ጊዜ እንደሚወስድ ከሰጉ፣ OAH ወረቀትዎን በፍጥነት መቀበሉን ለማረጋገጥ ከቀረቡት ሌሎች የማስገቢያ አማራጮች አንዱን መጠቀም ይችላሉ።
በኢሜል እንዴት ማስገባት ይቻላል
ወረቀቶችን ለ[email protected] በኢሜይል መላክ ይችላሉ።
ለማቅረብ በሌሎች በማንኛውም ኢሜይል የተላኩ ወረቀቶች ተቀባይነት አያገኙም።
ወረቀቶች በ PDF ቅርጸት እንደ አባሪ መሰቀል አለባቸው፣ እና የተያያዙት ወረቀቶች በአጠቃላይ ከ40 ገጾች በላይ መሆን አይችሉም። እንዲሁም፣ የጉዳይ ቁጥርዎን (አንድ ካለዎት) እና በኢሜይሉ የርዕስ መስመር ላይ ስለ ወረቀቱ አጭር መግለጫ ማካተት አለብዎት። ለሁሉም ሌሎች የኢሜይል ማቅረቢያ መስፈርቶችን የ OAH ደንብ 2841 ይመልከቱ። እንዲሁም የ OAH ደንቦችን በደንቦች እና ህጎች ገጽ ማግኘት ይችላሉ።
የኦንላይን ማስገቢያ ቅጽ በመሙላት ወረቀቶችን ማስገባት ይችላሉ። ወደ ቅጹ ለመሄድ ማስፈንጠሪያውን ጠቅ ያድርጉ፣ ሳጥኖቹን በአስፈላጊው መረጃ ይሙሉ፣ የወረቀቶችዎን ቅጂ በ PDF ቅርጸት ይስቀሉ፣ ከዚያም “ያስገቡ” የሚለውን ጠቅ ያድርጉ። መረጃው እና የተያያዙት ወረቀቶች ወዲያውኑ ወደ [email protected] ይሄዳሉ።
በመደበኛ የስራ ሰአታት ወቅት ኢሜይሎን ከላኩ፣ የገባበት ቀን በOAH ኢሜይል ማስገቢያ የገቢ መልዕክት ሳጥን የተመዘገበበት ቀን ነው። ነገር ግን ኢሜይሉን ከስራ ሰአታት ውጪ ከላኩ፣ OAH ወረቀትዎን በቀጣይ OAH ክፍት በሚሆንበት ቀን “እንደገባ” ይወስደዋል። ለምሳሌ፣ አርብ በ6:00pm ኢሜይል ከላኩ (ይህም ከ5:00pm መዝጊያ ሰአት በኋላ ነው)፣ OAH ወረቀትዎን በቀጣዩ ሰኞ “እንደቀረበ” ይወሰዳል (ወይም ሰኞ የበአል ቀን ከሆነ፣ ማክሰኞ)።
በፋክስ እንዴት ማቅረብ ይቻላል
ወረቀቶችን በፋክስ ወደ (202) 442-4789 መላክ ይችላሉ።
ፋክስዎን በመደበኛ የስራ ሰአታት ከላኩ፣ የገባበት ቀን OAH ፋክሱን በተቀበለበት ቀን ነው። ነገር ግን ከስራ ሰአታት ውጪ ፋክስ ከላኩ፣ OAH ወረቀትዎን በቀጣይ OAH ክፍት በሚሆንበት ቀን “እንደቀረበ” ይወስደዋል። ለምሳሌ፣ ወረቀትዎን አርብ በ6:00pm ፋክስ ካደረጉ (ይህም ከ5:00pm መዝጊያ ሰአት በኋላ ነው)፣ OAH ወረቀትዎን በቀጣዩ ሰኞ “እንደቀረበ” ይወስደዋል (ወይም ሰኞ የበአል ቀን ከሆነ፣ ማክሰኞ)።
በፋክስ OAH የተቀበላቸው ወረቀቶች ሙሉ እና የሚነበቡ መሆን አለባቸው። ካልሆኑ፣ OAH ወረቀቶቹን አይቀበልም። ከተቻለ፣ OAH ፋክሱ እንዳልተሳካ ለማሳወቅ እርስዎ ለማግኘት ይሞክራል። ከመጀመሪያ የሙከራዎ በ 3 የቀን መቁጠሪያ ቀናት ውስጥ የወረቀት ቅጂዎችን ካቀረቡ ወይም በተሳካ ሁኔታ በድጋሚ በፋክስ ከላኩ፣ OAH ወረቀቶቹ በመጀመሪያ ሙከራዎ ቀን “እንደቀረበ” ይወሰዳል።
ቅጣት እንዴት ይከፈላል
ለታክሲ ወይም ለኪራይ ተሽከርካሪ ጥሰት ትኬት ከደረስዎት(“ርዕስ 31” ጥሰት ተብሎ ይጠራል) እና ጥሰቱን “ማመን” እና መክፈል ከፈለጉ፣ የሞተር ተሽከርካሪ መምሪያ ድረገጽን ይጎብኙ እና ቅጣቱን ለመክፈል መመሪያዎቹን ይከተሉ። OAH የርዕስ 31 ጥሰቶችን በሚመለከት አከራካሪ ጉዳዮችን ይሰማል፣ ነገር ግን DMV በቀጥታ የቅጣት ክፍያዎችን ያስተናግዳል።
ከዲፖርትመንት ኦፍ ኮንሲዩመር ኤንድ ሬጉላቶሪ አፈይርስ (ዲ.ሲ.አር.ኤ.)) የስምምነት ማፍረስ ማስታወቂያ ከተቀበሉ እና ጥሰቱን “ማመን” እና መክፈል ከፈለጉ፣ የDCRA ድረገጽን ይጎብኙ እና ቅጣቱን ለመክፈል መመሪያዎቹን ይከተሉ። OAH DCRA NOIs በሚመለከት አከራካሪ ጉዳዮችን ይሰማል፣ ነገር ግን DMV በቀጥታ የቅጣት ክፍያዎችን ያስተናግዳል።
ለህግ ጥሰት ማስታወቂያ ወይም ለስምምነት መፍረስ ማስታወቂያ ከተቀበሉ እና ጥሰቱን ወይም ስምምነት ማፍረስዎን “ማመን” እና መክፈል ከፈለጉ፣ በሚከተሉት ማድረግ ይችላሉ፦
- Office of Administrative Hearings፣ 441 Fourth Street, NW, Suite 450 North, Washington, DC 20001 በፖስታ መላክ ወይም ቼክ ወይም የገንዘብ ማዘዣ በማምጣት። እባክዎ በቼኩ ወይም በገንዘብ ማዘዣው ላይ የማስታወቂያ ቁጥርዎን ያስቀምጡ። እንዲሁም የተቀበሉትን ማስታወቂያ ቅጂ ማካተት ቢችሉ ይጠቅማል፤ ወይም
- ቅጣትዎን ኦንላይን በOAH የክፍያ መቀበያ መክፈል። ይህን አማራጭ ለመጠቀም፣ OAH ጉዳይ ቁጥር ሊኖርዎት ይገባል። ማስታወቂያውን የሰጠዎት ድርጅት የማስታወቂያውን ቅጂ ለOAH ካላቀረበ፣ የ OAH ጉዳይ ቁጥር አይኖርዎትም። አሁንም ቅጣቱን መክፈል ይችላሉ ነገር ግን በቼክ ወይም በገንዘብ ማዘዣ መክፈል ይኖርብዎታል። የOAH ጉዳይ ቁጥር ካለዎት በመቀበያው የመጀመሪያ ገጽ ላይ ያለውን የመዝገብ ቁጥር ያስገቡ እና ክፍያውን ለማስገባት መመሪያዎቹን ይከተሉ። OAH ቅጣቶችን በባንክ አካውንት፣ በብድር ካርድ፣ ወይም ዴቢት ካርድ ይቀበላል።
ለመመለስ ምን ያህል ጊዜ እንዳለዎት ለማየት ማስታወቂያውን በጥንቃቄ ያንብቡ — ቅጣቱን ለመክፈል በትንሹ 14 ቀናት ሊኖርዎት ይችላል ክፍያዎ ከመጨረሻ ቀኑ በኋላ ከደረሰ፣ ከመጀመሪያ ቅጣት ጋር እኩል የሆነ ተጨማሪ መጠን ሊጣልብዎት ይችላል።
ችሎት ከነበርዎት እና ከአስተዳደር የህግ ዳኛ ቅጣት እንዲጣልብዎ የመጨረሻ ትዕዛዝ ከተቀበሉ፣ ከላይ በተብራሩት ተመሳአይ ዘዴዎች ቅጣቱን መክፈል ይችላሉ።
ቅጣት ሲከፍሉ ችግሮች ካጋጠሙዎት፣ የ OAH ጻሃፊ ቢሮን በ 202-442-9094 በመደወል እና ከዋናው ዝርዝር “3” በመጫን፣ ወይም በ [email protected] ኢሜይል በማድረግ ያነጋግሩ።
የርቀት ችሎት እንዴት መቀላቀል ይቻላል
ወደ Webex ችሎት መደወል፦
- ከWebex ችሎት ጋር ለመገናኘት፣ ወደ የOAH ምድብ የWebex ስልክ ቁጥር ይደውሉ፦ 1-202-860-2110። ከ202-አካባቢ ኮድ የስልክ ቁጥር የሚደውሉ ቢሆን እንኳን ከአካባቢው ኮድ በፊት “1” መደወል አለብዎት።
- ወደ Webex በሚደውሉበት ጊዜ፣ የሚከተለውን ይሰማሉ፦ “ወደ Webex እንኳን ደህና መጡ። የመዳረሻ ኮድዎን ወይም የስብሰባ ቁጥርዎን # በማስከተል ያስገቡ” በመርሃ ግብር ትዕዛዝ ላይ ያለውን ባለ 9 አሃዝ የመዳረሻ ቁጥር ያስገቡ። የOAH የመርሃ ግብር ትዕዛዝ ምን እንደሚመስል የሚያሳይ ምሳሌ ከታች አለ።
- የመዳረሻ ቁጥሩን ካስገቡ በኋላ፣ የሚከተለውን ይሰማሉ፦ “የተሳትፎ መለያ ቁጥርዎን # በማስከተል ያስገቡ የተሳትፎ ቁጥርዎን ከላወቁ፣ ለመቀጠል# ይጫኑ።” በቀላሉ #ይጫኑ።
- ከችሎቱ ጋር በተሳካ ሁኔታ እንደተገናኙ የሚያመለክት ድምጽ ይሰማሉ
የ Webex ችሎት ማጠቃለያ፦
- በችሎቱ ማጠቃለያ፣ በቀላሉ ይዝጉት። የ Webex ስብሰባውን ALJ ካጠናቀቀው፣ የሚከተለውን ይሰማሉ፦ “Webex ስለተጠቀሙ እናመሰግናለን። በ www.webex.com ድረገጻችንን ይጎብኙ።” ከዚያ በኋላ ጥሪው ይቋረጣል።
ሰብሳቢ ዳኛው ከመጀመሩ በፊት ወደ Webex ችሎት ይደውሉ፦
- ALJ ከመጀመሩ በፊት ወደ Webex ለመደወል ከሞከሩ፣ የሚከተለውን ይሰማሉ፦ “ስብሰባው ገና አልተጀመረም። የስብሰባው እንግዳ ከሆኑ፣ # በማስከተል፣ የእንግዳ ፒን ያስገቡ። እንግዳ ካልሆኑ፣ # ይጫኑ።” በቀላሉ #ይጫኑ።
- ከዚያ የሚከተለውን ይሰማሉ፦ “እንግዳው ስብሰባውን አልተቀላቀለም። እባክዎ ይጠብቁ።” ALJ Webex እስኪሚጀምር ድረስ ሙዚቃ ይጫወታል።
- ALJ Webex ሲጀምር፣ የሚከተለውን ይሰማሉ፦ “የተሳትፎ መለያ ቁጥርዎን # በማስከተል ያስገቡ የተሳትፎ ቁጥርዎን ከላወቁ፣ ለመቀጠል# ይጫኑ።” በቀላሉ #ይጫኑ። ድምጽ አይሰሙም፣ ነገር ግን በ Webex ችሎት ቀጥታ ስርጭት ውስጥ ይገባሉ።
ችግር መፍታት
- በመርሃ ግብር ትዕዛዙ በተዘረዘረው ቀን እና ሰአት ከWebex ችሎት ጋር መገናኘትዎን እርግጠኛ ይሁኑ።
- ተንቀሳቃሽ ስልክ ተጠቅመው ወደ ችሎቱ ከደወሉ፣ በሚደውሉበት ጊዜ የሲግናል ጥንካሬው ጠንካራ መሆኑን ያረጋግጡ። ሃይለኛ የጀርባ ጫጫታ የችሎት ተሳታፊዎች እንዴት እርስዎን እንደሚሰሙ ሊያስተጓጉል ስለሚችል ጸጥታ ካለበት አካባቢ መደወልዎን እርግጠኛ ይሁኑ።
- ከWebex ችሎት ጋር የመገናኘት ችግር ካጋጠምዎት፣ ለጉዳይዎ ክምችት የተመደቡ ህጋዊ ረዳቶች ጋር ለመገናኘት ከታች ያሉትን የስልክ ቁጥሮች ይጠቀሙ።
- የህዝብ ጥቅማጥቅሞች (DHS፣ SHEL፣ DHCF፣ DDS፣ ወዘተ): (202) 671-0055
- ፈቃድ መስጠት እና ህግ ማስከበር (DCRA፣ DOH፣ DOEE፣ ወዘተ): (202) 724-4904
- የህዝብ ስራዎች መምሪያ: (202) 727-8284
- የስራ አጥነት ጥቅማጥቅሞች: (202) 442-8175
- የህዝብ አገልግሎት ዘርፍ ሰራተኛ ማካካሻ, የሚከፈልባቸው የቤተሰብ ፈቃድ ጥቅሞች, ወይም የደመወዝ / የሰዓት ክርክር: (202) 442-7644
- ኪራይ ቤቶች: (202) 442-7644
- የ D.C. (ዲሲ) የህዝብ ትምህርት ቤቶች: (202) 442-7644
- ከOAH ሰራተኞች አናል ጋር መገናኘት ካልቻሉ፣ እና ችሎትዎ ካመለጥዎት፣ አዲስ የችሎት ቀን መጠየቅ ይችላሉ። ለአዲስ የችሎት ቀን ጥያቄዎን ለ [email protected] ይጠይቁ።